Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የሸበሌ ሪዞርት ግንባታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የሸበሌ ሪዞርት ግንባታ ላይ ያተኮረ ውይይት በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድና የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሀም በላይ (ዶ/ር) ከሚመለከታቸው የፕሮጀክቱና የክልሉ የስራ ሀላፊዎች ጋር በክልሉ በሚገነባው የሸበሌ ሪዞርት ግንባታ ዙሪያ ዛሬ መክረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የሸበሌ ሪዞርት ግንባታ አጠቃላይ ዲዛይንና የሚያካትታቸው መሠረተ ልማቶች ተጠቅሰዋል፡፡

የሚገነባው የሸበሌ ሪዞርት የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎችን፣ ሆቴሎችን፣ መናፈሻዎችን፣ የስብሰባ አዳራሾችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

የሸበሌ ሪዞርት ግንባታን በአንድ አመት ከግማሽ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.