Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከሶማሊያ እና ጅቡቲ የፖሊስ አዛዦች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከሶማሊያ እና ጅቡቲ የፖሊስ አዛዦች ጋር መክረዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ ÷ ከሶማሊያ ብሄራዊ ፖሊስ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሱሉብ አህመድ ፊን እና ከጅቡቲው ብሔራዊ ፖሊስ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዑመር ሁሴን ሀሰን ጋር ሽብርተኝነትና ሌሎች የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተቀናጀ የሦስትዮሽ ጥምረት ለመከላከል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የሦስቱን ሀገራት የፖሊስ መኮንኖች አቅም ማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያም መወያየታቸው ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይም የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በጅቡቲ ለመፈራረም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.