የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ ከደቡብ ሱዳን የፖሊስ አገልግሎት ኃላፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የፖሊስ አገልግሎት ኃላፊ ኢንስፔክተር ጀነራል ማጃክ አኬችንና ልኡካን ቡድናቸው ጋር ውይይት አድርገዋል ፡፡
በውይይታቸውም ÷ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተቀናጀ የሁለትዮሽ ጥምረት ለመመርመር በሚያስችል መልኩ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ልዑካን ቡድኑ በወንጀል ምርመራ ቢሮ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን ፥ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የወንጀል ምርመራን፣ የተጠርጣሪ አያያዝ፣ የዲ ኤን ኤ ላብራቶሪንና የዲጂታል ፎረንሲክ ምርመራን በአካል ተዘዋውረው መጎብኘታቸው ተገልጿል፡፡