የቀቤና ብሄረሰብ የባህል ማዕከል ተመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀቤና ልማት ማህበር የብሔረሰቡን ባህላዊ፣ ታሪካዊና የእምነት እሴቶች ባህል በሚገልፅ መልኩ በወልቂጤ ከተማ ያስገነባው ባህል ማዕከል አስመርቋል ፡፡
የባህል ማዕከሉ በቀጣይ በብሔረሰቡ ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክ ዙሪያ ለሚከናወኑ የጥናትና ምርምር ስራዎች ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ከመሆኑም በተጨማሪ ደረጃውን የጠበቀ ሙዚየም፣ የባህል አዳራሽ፣ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ቢሮዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት፣ ምሁራን፣ የልማት ማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።
3ኛው የቀቤና ብሄረሰብ የታሪክ፤ የባህልና የቋንቋ ሲምፖዚየም ቀጥሎ እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን በዕለቱ በብሄረሰቡ ምሁራን የተዘጋጁ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ይቀርባሉም ተብሏል።
በምንተስኖት ሙሉጌታ