Fana: At a Speed of Life!

በጂንካ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በአካባቢው መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በጂንካ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በአካባቢው መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነገረ፡፡

በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ከለሊት ጀምሮ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ኔሪ ተብሎ የሚጠራው ወንዝ እንዲሞላ ያደረገ ሲሆን ጎርፍም አስከትሏል።

የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ እንዳስታወቀው በዚህም ምክንያት ከተማውን የሚያገናኙ ሁለት ድልድዮች በጎርፍ ተወስደዋል።

መምሪያው መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በአደጋው በሰብል እና በእንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን ጨምሮ ገልጿል፡፡

በዚህም የአካባቢው ህብረተሰብ እና የዞኑ አመራሮች በቅንጅት የደረሰውን ጉዳት በማጣራት ላይ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.