Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም ከአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮምና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የአዲስ አበባ ስማርት ሲቲ” ኘሮጀክት አካል የሆነውን የመሰረተ ልማት ግንባታ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ  እና የአዲስ አበባ ከተማ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ሰለሞን አማረ ፈርመዋል፡፡

ኘሮጀክቱ  ኔትዎርክን በመዘርጋት በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ቢሮዎችን እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ከዋናው የዳታ ማእከል ጋር በቀላሉ በማስተሳሰር በ11 ክፍለ ከተሞች፣ በ120 ወረዳዎችና በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ 58 ቢሮዎችን እርስበርስ ማስተሳሰር የሚያስችል ነው።

280 ሚሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት ኘሮጀክቱ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

በቤተልሄም መኳንንት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.