Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ገንዘብ ድርጅት ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር ቅድሚያ ሰጥቶ ድጋፍ በሚያደርግባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ገንዘብ ድርጅት ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር ቅድሚያ ሰጥቶ የቴክኒክና የአቅም ግንባታ ድጋፍ በሚያደርግባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን ሚኒስቴሩ አስታወቀ።

የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በተገኙበት የዓለም ገንዘብ ድርጅት ለሚኒስቴሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የቴክኒክና የአቅም ግንባታ ድጋፎች ላይ ውይይት በማድረግ ድጋፍ የሚደረግባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ከድጋፎቹ መካከል የኤክሳይዝ ታክስ አተገባበርን ማዘመን፣ የሀገሪቱን የታክስ አስተዳደር ዲጅታላይዝ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻልና የኦዲት ስርዓቱ በአግባቡ እንዲመራና ውጤታማ እንዲሆን በቴክኖሎጂ መደገፍ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.