Fana: At a Speed of Life!

በአፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ የተመራ ልዑክ በጅግጅጋ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራ ልዑክ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡

አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገርንና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድን ያካተተ ልዑክ ከ597 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለውን የሶማሌ ክልል ምክር ቤት የሕንጻ ግንባታ ሂደትንም ጎብኝቷል፡፡

የምክር ቤቱ ሕንጻ ግንባታ በ2011 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን÷በ26 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡

የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ጣሂር አብዲ÷የፕሮጀክቱ የሕንጻ ግንባታ የተያዘለት በጀት ከ597 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑንና የግንባታው አፈጻጸም 85 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ግንባታው በቀጣይ 2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅም መግለጻቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ ልዑካን ቡድኑ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ አስተዋጽኦ ለማበርከት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውኗል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.