Fana: At a Speed of Life!

የመንግስታት ግንኙነት የጋራ የምክክር መድረክ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስታት ግንኙነት የጋራ የምክክር መድረክ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዘጋጅነት ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ እንደገለጹት ÷መድረኩ የኢትዮጵያ የመንግስታት ግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት ከተቋቋሙት የመንግስታት ግንኙነት መድረኮች አንዱ ነው።

በጋራ የምክክር መድረኩ በተለያዩ ምሁራን “የመንግስታት ግንኙነት ለጠንካራ ፌዴራል ስርዓት ግንባታ ያለው ሚና” እና “የመንግስታት ግንኙነት ተሞክሮ በኢትዮጵያ እና ቀጣይ አቅጣጫ” በሚሉ ርዕሶች ጽሁፎች ቀርበው ምክክር እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።

በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል አፈ-ጉባዔዎችና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እንደሚሳተፉና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ እንደሚመክሩ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.