Fana: At a Speed of Life!

የፊታችን ሰኞ በዎላይታ ዞን የሕዝበ ውሣኔ ምርጫ ድምፅ የመስጠት ሂደት ይከናወናል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዎላይታ ዞን የፊታችን ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ. ም. የሕዝበ ውሣኔ ምርጫ ድምፅ የመስጠት ሂደትን እንደሚያስፈጽም አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በዎላይታ ዞን የሚያስፈጽመውን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ ምርጫ የድምፅ መስጠት ቀንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሠረት በዕለቱ የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ ድምፃቸውን መስጠት እንዲችሉ እንዲሁም የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወን ለማስቻል ቦርዱ የተለያዩ ተግባራት ተፈጻሚ እንዲሆኑ አሳስቧል፡፡

ተፈጻሚ የሚደረጉትን ጉዮችም የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የሥነ ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ቀጥለው የተጠቀሱት ጉዳዮች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ለመንግሥታዊና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ማሳወቁን ቦርዱ ገልጿል፡፡

  • ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በዞኑ የሚገኙ የፌዴራልና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ. ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣
  • ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጠት ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በዞኑ የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ. ም. ዝግ እንዲያደርጉ፣
  • የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ማለትም ሆስፒታሎችን ጨምሮ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት …ወ. ዘ. ተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን የሚችሉ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።
  • የትራንስፖርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም በዞኑ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችንና ዕቅዶችን እንዳይዙ እንዲሁም እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.