የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ችግኝ ተከሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኡራ ወረዳ አምባ 11 ቀበሌ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናወኑ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና በብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሚንስትር ሳዳት ነሻ÷ ለሦስተኛ ዙር የምንተክለው የአረንጓዴ ዐሻራ ማኖር ፕሮግራም ከሀገራችንና ቀጣናችን አልፎ በዓለም ላይ ድንቅና ወደፊት ለትውልድ የሚተላለፍ ተግባር ነው ብለዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢሳቅ አብዱልቃድር÷ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በብዛትም በጥራትም መትከል እና መንከባከብ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በክልሉ በዚህ የክረምት ወራት 55 ሚሊየን የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት መደረጉን የብልጽግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል፡፡