Fana: At a Speed of Life!

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 14 የድምፃውያን ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፋና ቴሌቪዥን የሚዘጋጀው ተወዳጁ የፋና ላምሮት የባለ ተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር 14ኛ ምዕራፍ ተጀመረ።

ፋና ላምሮት ከአዳዲስ ተወዳዳሪዎችና ባለተሰጥኦዎች ጋር በቀጥታ ስርጭት የጀመረ ሲሆን ፥ በሁለት ምድብ የተከፈሉት የምዕራፍ 14 ተወዳዳሪዎች 12 ናቸው፡፡

ለዘጠኝ ሣምንታት የሚቆየው የምዕራፍ 14 የፋና ላምሮት የባለተሰጥዖ ድምጻውያን ውድድር መጨረሻ የሚቀሩ አራት የምዕራፉ ተፋላሚዎች እንደየደረጃቸው በድምሩ የ1 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡

አንደኛ ደረጃን ላገኘ የ400 ሺህ ብር፣ 2ኛደረጃ 300 ሺህ ብር፣ 3ኛ ደረጃ 200 ሺህ ብር እና 4ኛ ደረጃን ያገኘ የ100 ሺህ ብር ሽልማት አሸናፊ ይሆናሉ፡፡

በተጨማሪም የፍጻሜ ተወዳዳሪዎቹ በጉጉት ለሚጠበቀው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

በቀጥታ ስርጭት የተጀመረው የምዕራፍ 14 የፋና ላምሮት ውድድር ተመልካቾች ወደ 8222 አጭር የፅሁፍ መልዕክት በመላክ ለሚደግፉት ተወዳዳሪ ድምፅ መስጠት ይችላሉ።

የምዕራፍ 13 ፋና ላምሮት የባለተሰጥዖ ድምጻውያን ውድድር ፍጻሜ ከሁለት ሣምንት በፊት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ተወዳዳሪዎች ራሳቸው በመረጧቸው እና ዳኞች በመረጡላቸው ሙዚቃዎች ተፈትነው ከአንድ እስከ አራት ለወጡት ተወዳዳሪዎቹ በአጠቃላይ የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በረከት ደሞዝ በ13ኛው ምዕራፍ አሸናፊ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

#Ethiopia #FanaLamrot

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.