Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ከ“ሃይፈር ፕሮጀክት ኢንተርናሽናል” ጋር በጥምረት ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመሥኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ “ሃይፈር ፕሮጀክት ኢንተርናሽናል” ጋር በጥምረት ለመሥራት ሥምምነት ተፈራረመ፡፡

ሥምምነቱን የመሥኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) እና የ”ሃይፈር ፕሮጀክት ኢንተርናሽናል” ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ሶሪታ ሳንዶሻ ተፈራርመዋል፡፡

አይሻ መሃመድ (ኢ/ር )÷ኢትዮጵያ የአየር ንብረትን መሰረት ያደረጉ ዘላቂ የልማት ሥራዎችን ለመተግበር በምታደርገው ጥረት ከ”ሃይፈር ፕሮጀክት ኢንተርናሽናል” ጋር የተደረገው የትብብር ሥምምነት ትልቅ አቅምን የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

ሥምምነቱ የቆላማና አርብቶ አደር የልማት ስትራቴጂ ለመንደፍ እንዲሁም በአነስተኛ አርሶ አደሮች ደረጃ የእንስሳት ተዋፅኦ ሐብቶችን ገበያ-መር ለማድረግ እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

የገበያ ሰንሰለቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመዘርጋት እና በግሉ ዘርፍ የሚመራ አዋጭ የመስኖ ፕሮግራሞችን ለመተግበርም ትልቅ ሚና ይኖረዋልም ተብሏል፡፡

ሶሪታ ሳንዶሻ በበኩላቸው ÷ ከሚኒስቴሩ ጋር በትብብር ለመሥራት በመስማማታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

“ሃይፈር ፕሮጀክት ኢንተርናሽናል”÷ ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ለመሆንና ዘላቂ የገበያ ትሥሥሮችን ለመዘርጋት ዓላማ ሰንቆ ሚኒስቴሩ በሚያከናውናቸው ተግባራት በዘላቂነት አብሮ ለመሥራት ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡

“ሃይፈር ፕሮጀክት ኢንተርናሽናል” ለትርፍ ያልተቋቋመና ከአነስተኛ አርሶ አደሮች ጋር በተያያዘ ረሃብንና ድኅነትን በዘላቂነት ለማስወገድ የሚሠራ ተቋም ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.