Fana: At a Speed of Life!

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር ) ከፈረንሳይ ንግድ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ንግድ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር ) ÷ለልዑካን ቡድኑ አባላት ስለ ምዕራፍ ሁለት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ይዘትና ዝግጅት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተለይም መንግስት የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማሳደግ በማሻሻያው ያስቀመጣቸውን ቁልፍ ሃሳቦች አስረድተዋል፡፡

የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የኢንቨስትመንት ተሳትፎም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የፈረንሳይ ንግድ ም/ቤት ልዑካን ቡድን አባላት በበኩላቸው÷ በርካታ የፈረንሳይ ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

በቀጣይም ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.