የሩሲያ-አፍሪካ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሔደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ ማህበር (ዩኤንኤ-ሩሲያ) ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሩሲያ-አፍሪካ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሔደ ነው።
በፎረሙ ላይ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ይቭጄኒ ተረኺን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ተወካዮች፣ የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ከተሞች ተወካዮች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እየተሳተፉ ነው።
ፎረሙ “የከተሞች የወደፊት ዘላቂ ልማት የልምድ ልውውጥ እና አጋርነት ለጋራ ግቦች” በሚል መሪ ቃል ነውበአዲስ አበባ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፎር አፍሪካ የስብሰባ ማዕከል እየተካሔደ የሚገኘው፡፡
በመድረኩ በአፍሪካ እና በሩሲያ በሚገኙ ክልሎች እና በከተሞች የሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል ልማት እና ትብብር ዙሪያ ውይይቶች እና ገለጻዎች እየተካሔዱ ነው።
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ይቭጄኒ ተረኺን÷ሞስኮን ጨምሮ የተለያዩ የሩሲያ ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ በመሆን ከፍተኛ እድገት እያስገኙ እንደሆነና ለአፍሪካ ከተሞችም ልምዳቸውን ማጋራት እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ዘላቂ የከተማ ልማትን በቁጥር ሳይሆን ተጨባጭ በሆነ በሚታይ እድገት መለከታ ይገባልም ብለዋል።
አምባሳደሩ አክለውም አዲስ አበባ ባለፉት አራት ዓመታት ከፍተኛ ለውጥ እያስመዘገበች እንደሆነ ገልጸው ሀገራቸውም ለውጡን እንደምትደግፍ ተናግረዋል።
በመሳፍንት ብርሌ እና ዘመን በየነ