የኮንሶ የማንነት መገለጫ የሆነው የ”ኾራ አታ ኾንሶ” የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘጠነኛው የአለም ቅርስ ባለቤት የሆነው የኮንሶ ማንነት መገለጫ “ኾራ አታ ኾንሶ” የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ÷ “ኾራ አታ ኾንሶ” በዓል መታሰቢያ ቀን የሚከበረው አባቶች ያወረሱንን ባሕል ወግና ልማድ ለማስቀጠልና ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ ነው ብለዋል።
ዋና አስተዳዳሪው ዞኑ በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መስህቦች ባለቤት መሆኑን፣በጠንካራ የስራ ባህልና አስደናቂ መልክአምድር አቀማመጥ በአለም ቅርስነት የተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።
የሲምፖዚየሙ ዓላማ ባህሉ ሳይበረዝ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎችም በአለም ቅርስነት የተመዘገበውን ቅርስ በእንክብካቤ ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል።
በመለሰ ታደለ