ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጋራ መኖሪያ ቤት በህብረት ስራ ማህበር የቤት ግንባታን አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመኖሪያ ሕብረት ስራ ማሕበራት የተደራጁ የመኖሪያ ቆጣቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት ግንባታ መርሐ ግብርን አስጀምረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በ54 የመኖሪያ ሕብረት ስራ ማሕበራት የተደራጁ ከ4 ሺህ በላይ የጋራ የመኖሪያ ቤት ቆጣቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ከንቲባ አዳነች÷ የነዋሪው ቀዳሚ ጥያቄ የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ አዳዲስ አማራጭ አሰራሮች እና ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡
የጋራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቆጣቢ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጀውን ይህን አማራጭ ተጠቅመው በማህበር በመደራጀት እና በመቆጠብ የቤት ባለቤት መሆን እንደሚችሉም አስታውቀዋል፡፡