Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች የጤና አውደ ርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የጤና አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የጤና አውደ ርዕይ በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል፡፡

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ÷ አውደ ርዕዩ የሕብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንና ኢትዮጵያ በዘርፉ ያለችበትን ደረጃ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የሕብረተሰብ ጤና ከምርት እና ምርታማነት ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንዳለው ገልጸው÷በዚህ ረገድ በጤናው ዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ አበረታች ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አንስተዋል።

በሚኒስቴሩ የሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡሞድ በበኩላቸው÷ አውደ ርዕዩ ታዳጊዎች በጤናው ዘርፍ ለመሰማራት ራዕይ ሰንቀው እንዲሰሩ መነሳሳት ይፈጥራል ብለዋል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የኪነ-ጥበብ ሙያ ዘርፍ ማህበራት እና የየካቲት ሆስፒታል ሰራተኞች አውደ ርዕዩን ጎብኝተዋል፡፡

ጎብኚዎቹ ኢትዮጵያ ከሀገር በቀል ዕውቀት እስከ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሕክምና ቴክኖሎጂ የደረሰችበትን የጤና እምርታ በማየታቸው እንደተደሰቱ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.