Fana: At a Speed of Life!

ተስፋ ያላቸው አዳጊዎች ወደ እግር ኳሳችን እየመጡ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀትና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት ተስፋ ያላቸው አዳጊዎች ወደ እግር ኳሳችን እየመጡ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተገኝተው በሴካፋ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሶማሊያ ጋር ሲጫወት በአካል ተገኝተው ማበረታታቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ ያቀረቡትን ይፋዊ ጥያቄ ተከትሎ መንግሥት በየአካባቢው ከትናንሽ እስከ ግዙፍ ስታዲየሞችን እየገነባ እንደሚገኝ አስታውሰዋል።

ከመሠረተ ልማት ባሻገር ደግሞ የኢትዮጵያውያንን እግር ኳስ ወዳድነት የሚመጥን እና መልካም ስማችንን ከፍ የሚያደርግ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተጀምረዋል ብለዋል።

‘የጉዞ 2029 ፕሮጀክት’ የሆነው ከ17 ዓመት በታች ቡድናችንም ትልቅ ተስፋ ያለውና የኢትዮጵያ ወጣቶችና አዳጊዎች ኳስ ጨዋታ እንደሚችሉ እንዲሁም ለአህጉራዊ ዋንጫው ከታች የጀመርነው ዝግጅትም ፍሬ እያፈራ መሆኑን ተመልክተንበታል ነው ያሉት።

ለቡድኑ እዚህ መድረስ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፣ ለአሰልጣኝ አባላት፣ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች ምስጋና ያቀረቡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የአዳጊ ቡድኑ አባላት በስካሁኑ የውድድር ሂደት ላስመዘገቡት ውጤት በርቱ ማለት እፈልጋለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.