Fana: At a Speed of Life!

ኢኮኖሚውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ተቋማት በትብብር እንዲሠሩ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ሁሉም ተቋማት በትብብር ሊሰሩ ይገባል ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ  መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡

ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተባበሩት የንግድና ልማት ኮንፈረንስ ጋር በመተባበር በሚቀጥሉት 7 ዓመታት የሚተገበረውን ሁሉን አቀፍ የምርታማነት የአቅም ማሳደጊያ ፕሮግራም ማስጀመሪያ አካሂዷል፡፡

አቶ መላኩ አለበል በቅንጅት መስራት ውጤታማ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አንዱ ማሳያ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ለንቅናቄው  ቀጣይነትና ውጤታማነት ተቋማት የሚመሯቸው አምስት ክላስተሮች መቋቋማቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ለሁሉም ክላስተር የስራ ድርሻ በጥናት ተለይቶ የተሰጠና የስራ ሂደቱ በየጊዜው የሚገመገም በመሆኑ የተሻለ ለውጥ እየተመዘገበ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)÷ የሰው ሀብት ልማትና ቅንጅታዊ ትስስር ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት ቀዳሚውን ድርሻ እንደሚወስዱ  አስረድተዋል፡፡

ሁሉን አቀፍ የምርታማነት የአቅም ማሳደጊያ ፕሮግራም  ከሀገራችን ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች ጋር የተጣጣመና  እቅዶቻችንን በተሻለ ለመፈጸም የሚኖረው አቅም ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.