Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፋዊ አጋርነትን ለማጠናከር የፖለቲካ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፋዊ አጋርነትን እና ትብብርን ለማጠናከር የፖለቲካ ቁርጠኝነት አስፈላጊ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ ገለጹ።

በአምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አዘርባጃን ባኩ ከተማ እየተካሄደ ባለው የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ የሚኒስትሮች ጉባዔ እየተሳተፈ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው የንቅናቄውን የሚኒስትሮች ስብሰባ እያካሄድን ያለነው ዓለማችን ውስብስብ እና በርካታ ፈተናዎች በተጋረጡባት ወቅት ነው ብለዋል፡፡

ስለሆነም በተለመደው ሳይሆን አዳዲስ ዕይታ እና ሐሳቦች ያስፈልጉናል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ሠላም የሰፈነበት እና የበለጸገ ዓለም ለመፍጠር ም÷ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓቱ እንዲሻሻል ጠይቀዋል።

በአየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያ ተግባራዊ ያደረገችውን የአረንጓዴ ልማት እንዲሁም በሠላም ማስከበር የተጫወተችውን ሚና አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የገለልተኛ ሀገራት መሥራች አባል እንደመሆኗ÷ የወደፊት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል መርኅላይ ያተኮረ እና ውጤታማ የባለብዙ ወገን ተሳትፎ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.