Fana: At a Speed of Life!

በተጠናቀቀው በጀት በአዲስ አበባ ከ416 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት በመዲናዋ ከ416 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

 

ሶስተኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሁለተኛ ዓመት የስራ ዘመን አራተኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማዋ ምክር ቤት የአስተዳደሩን የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

 

በዚህም በ2015 በጀት ዓመት ለ464 ሺህ የስራ ፈላጊዎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ416 ሺህ 999 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።

 

እንደ ኢዜአ ዘገባ ከተፈጠሩት የስራ እድሎች መካከል 375 ሺህ 299 ቋሚ እና 41 ሺህ 700 ደግሞ ጊዜያዊ መሆናቸውን አመላክተዋል።

 

የስራ እድል ፈጠራ አፈጻጸሙ አበረታች ቢሆንም ካለው ፍላጎት አኳያ አሁንም ብዙ መስራት ይጠይቃል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.