Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችና ጋምቤላ ክልሎች የት/ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ሕዝባዊ ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች እና ጋምቤላ ክልሎች የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ሕዝባዊ ንቅናቄ መድረክ ተጀምሯል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ÷ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ቴፒ መለስተኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በይፋ ዛሬ ተጀምሯል።

በመርሐ ግብሩ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ተገኝተዋል፡፡

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ÷ በክልሉ በትምህርት ልማት ዘርፍ በርካታ ስብራቶች መኖራቸውን ጠቁመው÷ችግሩን ለመቅረፍም በቆራጥነት መነሳትና በቅንጅት መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በትምህርት ላይ መሥራት በሰው አዕምሮ ላይ የማይነጥፍ ሐብት ማስቀመጥ ነው ብለዋል፡፡

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ ያሉንን ሐብቶች ወደ ውጤት ለመቀየር የሰለጠነና የበቃ የሰው ኃይል ወሳኝ ነው ብለዋል።

ይህን ዕውን ለማድረግም የትምህርትቤቶችን የመሠረተ ልማት ችግሮች ኅብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመቀናጀት መቅረፍ ይገባል ብለዋል።

በተመሳሳይ በጋምቤላ ንቅናቄውን ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ÷ በክልሉ ከደረጃ በታች የሆኑ ከ600 በላይ ትምህርት ቤቶች እንደሚጠናከሩ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሴ ጋጀት÷ በክልሉ ያሉ የትምህርት ተቋማት ያሉባቸውን ችግሮች እልባት ለመስጠትና የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ይህ ንቅናቄ ወሳኝ ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.