አፍሪካዊያንም ካለፉት ችግሮቻችን ተምረን ጥቅም ላይ ያልዋለውን ጉልበት ወደ ሃብት መቀየር ይገባናል-ሙፈሪሃት ካሚል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካዊያንም ካለፉት ችግሮቻችን ተምረን ጥቅም ላይ ያልዋለውን ጉልበት ወደ ሃብት መቀየር ይገባናል ሲሉ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ፡፡
የአፍሪካ የሥራ ፎረም የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ለኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማትና ማስፋፋት ያለው መልካም ዕድሎችና ፈተናዎች በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል÷አፍሪካ በውስጧ እምቅ ሃብት ያላት አህጉር በመሆኗ የመልማት እድሎችን አፍሪካውያን በጋራ መጠቀም ይኖርብናል ብለዋል፡፡
የስራ ባህል ለውጥ ላይ ትኩረትን ያደረጉ ሃገራት ዛሬ ላይ ስኬት ላይ ደርሰዋል ያሉት ሚኒስትሯ÷አፍሪካዊያንም ካለፉት ችግሮቻችን ተምረን ጥቅም ላይ ያልዋለውን ጉልበት ወደ ሃብት መቀየር ይገባነናል ብለዋል።
3ኛ ቀኑን የያዘው የአፍሪካ የስራ ጉባኤ አንዱ መርሃ ግብር በሆነው በዚህ መድረክ የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክስ ንግድ ቡድን ተሳታፊዎች እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
በይስማው አደራው