Fana: At a Speed of Life!

በመኪና አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጌዴኦ ዞን ይርጋ ጨፌ ወረዳ በተከሰተ የመኪና አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

አደጋው ዛሬ ከያቤሎ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በወረዳው ቆንጋ ቀበሌ በመገልበጡ የደረሰ  ነው፡፡

በአደጋው እስከ አሁን የ9 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን÷ ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ተሳፋሪዎች መኖራቸውን ከጌዴኦ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.