ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ችግር በበርካታ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ችግር የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው ፥ ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ያጋጠመውን ችግር ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው፡፡
ችግሩ እንደተቀረፈም የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎቱ ወደነበረበት እንደሚመለስ አስታውቋል፡፡