አቶ ደመቀ መኮንን በአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ገቡ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ43ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ገብተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጀሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፥ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ባጫ ደበሌን ጨምሮ ሌሎች የኬንያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ስብሰባው “የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ ከሐምሌ 6 እስከ 8 ቀን 2015 ድረስ ይካሄዳል።
በስብሰባው ላይ የህብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የሕብረቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ቀጣናዊ የአፍሪካ ተቋማት ኃላፊዎች እና እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።