ጎንደር አራዳ የኢትዮጵያ የክለቦች ሻምፒዮና ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በሻምፒና ውድድሩ ከተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ 31 ክለቦች መሳተፋቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በማጠቃለያ ውድድሩ ጎንደር አራዳ ደምበጫ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ የኢትዮጵያ የክለቦች ሻምፒዮና ሆኗል፡፡
ጎንደር አራዳ እና ደምበጫ ከተማ ቀደም ሲል ወደ አንደኛ ሊግ ማደጋቸው ይታወሳል፡፡