በጎፋ ዞን በወንጀል የተጠረጠሩ 4 የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎፋ ዞን በወንጀል የተጠረጠሩ 4 የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡
የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀ አጥናፉ እንደተናገሩት÷ ፖሊሶቹ ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 7 ሰዓት ላይ በዞኑ ላንቴ ቀበሌ እና ቡልቂ ከተማ ኬላ ጥበቃ ላይ ተመድበዉ በስራ ላይ በነበሩበት ወቅት በህገወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ተጭኖ ሲወጣ የነበረን የአፈር ማዳበሪያ በቁጥጥር ስር ካዋሉ በኋላ ከግለሰቦች ጋር በመደራደር በመልቀቅ ተጠርጥረዋል።
በተሽከርካሪ ተጭኖ ከአካባቢዉ ሊወጣ የነበረዉ የአፈር ማዳበሪያ ሁለቱን የጥበቃ ኬላዎች አልፎ በዞኑ ፖሊስ መያዙን አዣዡ አስረድተዋል፡፡
ፖሊስ ባደረገው ክትትልም አራቱ ፖሊሶች የተጣለባቸውን ሃለፊነት ወደ ጎነ በመተው በጥቅም በመታለላቸው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል፡፡
በቁጥጥር ስር የዋሉት እነዚህ አራቱ የፖሊስ አባላት በፈፀሙት ግድፈት ምርመራ ተጣርቶባቸዉ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ መሆኑንም ነው የጠቆሙት፡፡
የፖሊስነት ሙያ ክቡር መሆኑን የገለፀው የዞኑ ፖሊስ፤ ሙያቸዉን ተገን አድርገዉ በመሰል ተግባር ዉስጥ የሚገቡ አባላት ካሉ ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡