Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከኬንያ ፣ ሩዋንዳ እና ናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ እና ከናይጄሪያ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዳሙ ኢብራሂም ጋር በኬንያ ተወያይተዋል።

በተመሳሳይ አቶ ደመቀ ከኬንያ የውጭ የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር አልፍሬድ ንጋንጋ ሙቱዋ (ዶ/ር) ጋርም መምከራቸውን ገልጸዋል።

በውይይታቸውም በተለይ የጋራ ድንበር አስተዳደር ኮሚሽን እንዲጠናከር እና የሽብርተኝነትን አደጋ ለመከላከል በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

አቶ ደመቀ ከሩዋንዳ እና ናይጀሪያ የውጭ ጉዳይ እና ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ያደረጉት ውይይት ፥ በሀገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ ኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው 43ኛው የአፍሪካ ኀብር የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.