Fana: At a Speed of Life!

የኬር ኦድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው የኬር ኦድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

በ15 ኪሎ ሜትር የሴቶች ውድድር ጉተኒ ሻንቆ  ቀዳሚ ስትሆን መብራት ግደይ እና ፀሀይ ሀይሉ   ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

በወንዶች15 ኪሎ ሜትር ጭምዴሳ ደበሌ በቀዳሚ ሲሆን÷ ሉሌ ላቢሳ ሁለተኛ  እንዲሁም ጎሳ አምበሉ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።

ውድድሩን ላሸነፉ አትሌቶች ከ25  ሺህ እስከ 75 ሺህ ብር ሽልማት የተበረከተ ሲሆን÷ በዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ 20 ሺህ  የህብረተሰብ ክፍሎች የታደሙት ሲሆን÷  385  አትሌቶች  ደግሞ ተሳትፈዋል።

ከ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ  ጎን ለጎን የ1 ኪሎ ሜትር ሜትር  የአካል ጉዳተኞች ዊልቸር ውድድር ተካሄዷል።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.