Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል ዘመቻ ተጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል ዘመቻ ተጀምሯል።

የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ሃገሪቱ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

እስከ ምሽት 12 ሰአት ድረስ በሚቆየው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 9 ሺህ 500 ቦታዎች ካርታ (ጂኦስፓሻል ማፕ) እንደተዘጋጀላቸው ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በሁለተኛው ምዕራፍ (ከ2015 እስከ 2018 ዓ.ም) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 25 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል አቅዳ እየሠራች ትገኛለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሁለተኛውን ምዕራፍ የመጀመሪያ ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ሰኔ 1ቀን 2015 ዓ.ም በአፋር ክልል ማስጀመራቸው ይታወሳል።

በአጠቃላይ የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር እንደየአካባቢው ሥነ-ምኅዳራዊ ሁኔታ ቢወሰንም እስከ መስከረም 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚዘልቅ ተጠቅሷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.