ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የፖሊት ቢሮ አባል እና ከፓርቲው የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ዋንግ ዪ ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው ከቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ የተላከላቸውን መልዕክት መቀበላቸውን አስታውቀዋል።
በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ትብብር አጠናክራ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።