Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል የ2016 በጀትን ከ137 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በማድረግ አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የ2016 በጀት 137 ቢሊየን 408 ሚሊየን 472 ሺህ 187 ብር ሆኖ ጸደቀ።

የክልሉ ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ ነው በጀቱ ያጸደቀው።

ከጠቅላላው የ2016 በጀት የክልሉ የልማት ፋይናንስ ውስጥ 89 ቢሊየን 279 ሚሊየን 467 ሺህ ብር ወይም 65 በመቶ በክልሉ የሚሰበሰብ ገቢ ሆኖ መታቀዱ ተገልጿል ።

በተጨማሪም የተጓደሉ የዳኞች እና የንዑስ ዳኞች አስተዳደር አባላት ምርጫም ተካሂዷል።

በክልሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ግርማ የሽጥላ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው እርሳቸውን የሚተኩ ሌላ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል እንዲሆኑ ተመርጠዋል።

እጩ ዶክተር አብዱ ሁሴን በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ተሹመዋል።

በተጨማሪም 13 የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በምክር ቤቱ ተሹመዋል።

አንድ ዳኛ የስነ ምግባር ጉድለት ስለተገኘበት የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በወሰነበት ውሳኔ መሰረት ከዳኝነት እንዲሰናበት ተደርጓል።

ለ3 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአማራ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤም ተጠናቅቋል።

 

 

 

 

ለይኩን አለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.