Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 3 የዳቦ ፋብሪካዎችን መርቀው አገልግሎት አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 3 የዳቦ ፋብሪካዎችን መርቀው አገልግሎት አስጀመሩ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ዛሬ ለከተማችን ነዋሪዎች ተጨማሪ ብስራት የሆኑ 3 የዳቦ ፋብሪካዎችን መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል” ብለዋል።
የዳቦ ፋብሪካዎቹ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ነዋሪዎችን ኑሮ በመደጎም ረገድ ትልቅ ድርሻ እንደሚኖራቸው ገልጸው፤ ፋብሪካዎቹ በቀን እስከ 1 ሚሊየን ዳቦ እንደሚያመርቱና የመዲናዋን ዕለታዊ የዳቦ ማምረት አቅምን ወደ 5 ነጥብ 2 ሚሊየን እንደሚያሳድጉ ተናግረዋል።
ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር የዳቦ ፋብሪካዎቹን ገንብተው ለአገልግሎትላበቁት አልኸይር የዳቦ ፋብሪካ፣ ዩኒቲ የዳቦ ፋብሪካ እና ዮናን የዳቦ ፋብሪካ በመዲናዋ ነዋሪዎች ስም ከንቲባዋ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በተመሳሳይም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተገነቡ 2 የምገባ ማዕከላት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል፡፡
የምገባ ማዕከላቱ ለአገልግሎት መብቃት በመዲናዋ የሚገኙ የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከሎችን ቁጥር 19 የሚያደርሱ ሲሆን ከ32 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወገኖች እንደሚመገቡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.