Fana: At a Speed of Life!

በሞናኮ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት አሸነፈ።

በውድድሩ በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

ውድድሩን አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት በ12 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ ከ18 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በቀዳሚነት አጠናቋል።

ወጣቱ አትሌት በሪሁ አረጋዊ ደግሞ በ12 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ ከ58 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ እንዲሁም ጥላሁን ኃይሌ በ12 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ ከ70 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የወንዶች ውድድር ደግሞ አትሌት አብርሀም ስሜ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው አራተኛ ሆኖ አጠናቋል።

በምሽቱ የአንድ ማይል የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.