Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ዳሬሰላም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ታንዛንያ ዳሬሰላም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

በአቶ ደመቀ የተመራ ልዑክ ታንዛንያ በሚካሄደው የአፍሪካ የሰው ኃይል ልማት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ዳሬሰላም መግባቱ ይታወቃል።

በጉባኤው ላይ የሚሳተፈው ልዑክ በዳሬሰላም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መጎብኘቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አካል የሆነ ችግኝ ተከላ ማካሄዳቸውም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.