የሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ነገ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴንት ፒተርስበርግ ሚካሄደው የሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ነገ እንደሚጀመር የሩሲያ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ክሬምሊን አስታውቋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ መድረክም 49 የአፍሪካ ሀገራት እንደሚሳተፉ ነው የተገለጸው።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ረዳት ዩሪ ኡሽኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት÷ በሁለተኛው የሩሲያ -አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ፕሬዚዳንት ፑቲን የ17 ሀገራት መሪዎች በሚሳተፉበት የጠዋቱ መርሐ ግብር ላይ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
ከ49ኙ የአፍሪካ ሀገራት 17ቱ በመሪዎቻቸው ሲወከሉ አምስት ሀገራት በምክትል ፕሬዚዳንቶቻቸው፣ አራት ሀገራት በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና አንድ ሀገር ደግሞ በፓርላማ መሪዋ እንደምትወከል ተመላክቷል፡፡
ሌሎች 17 ሀገራት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ወይም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው የሚወከሉ ሲሆን፥ አምስት ሀገራት እንዲሁ በአምባሳደሮቻቸው እንደሚወከሉ ተገልጿል፡፡
ጉባኤው “ለሰላም ደህንነት እና ልማት” በሚል መሪ ቃል የሚደረግ ሲሆን የጉባዔው አላማ የሩሲያ-አፍሪካን ትብብር ማሳደግ እና የአፍሪካ መንግስታትን ሉዓላዊነት ማጠናከር ነው ተብሏል፡፡
ከጉባዔው ጎን ለጎን የሩሲያ እና አፍሪካን ኢኮኖሚያዊ እና ሰብዓዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ፎረሞች ይደረጋሉ መባሉን አር ቲ በዘገባው አመላክቷል፡፡
ሌሎች 17 ሀገራት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ወይም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ይወከላሉ የተባለ ሲሆን አምስት ሀገራት እንዲሁ በአምባሳደሮቻቸው እንደሚወከሉ ተገልጿል፡፡
ጉባኤው “ለሰላም ደህንነት እና ልማት” በሚሉ መሪ ቃሎች የሚደረግ ሲሆን የጉባዔው አላማ የሩሲያ-አፍሪካን ትብብር ማሳደግ እና የአፍሪካ መንግስታትን ሉዓላዊነት ማጠናከር ነው ተብሏል፡፡