Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ከክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ከ11 ዞኖችና ፖሊስ መምሪያዎች ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ በክልሉ የ2016 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ በ2015 የሥራ አፈጻጸም ላይ የታዩ ክፍተቶች እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የክልሉን ሕዝብ ሰላምና መረጋጋት በተለይም÷ በድንበር አካባቢዎች ፀጥታን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለውይይ ተሳታፊዎች አቅጣጫ መሰጠቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.