ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሳውላ ከተማ ለሚገነባው ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረተ ድንጋይ አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ለሚገነባው ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ።
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ የመሰረተ ድንጋዩን አኑረዋል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ሙሉ ወጪ የሚሸፈነው ሠዎች ለሠዎች በተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት መሆኑም ተገልጿል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠ በኋላ በቅጥር ግቢው ችግኝ የመትከል ስነ-ስርዓት መካሄዱን በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ክልል ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።