ለቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ገንዘብ የ23 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ክፍተት መኖሩ ተመለከተ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት የሚፈለገውን ግብዓት ለማሟላት ከሚያስፈልገው ገንዘብ የ23 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ክፍተት መኖሩን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
እንደሀገር በየዓመቱ ለቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ግብዓት ማሟያ ከሚያስፈልገው 41 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር÷ 2 ሚሊየን ዶላር በመንግስት 15 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ከአጋር ድርጅቶች መገኘቱ ተመላክቷል፡፡
ይሁን እንጅ ከሚያስፈልገው በጀት አንጻር የ23 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ክፍተት መፈጠሩን ነው በሚኒስቴሩ የሥነ- ተዋልዶ፣ የቤተሰብ ዕቅድ እና የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች አገልግሎት ዴስክ ከፍተኛ ባለሙያ ገነት ድረስ የገለጹት፡፡
ክፍተቱ የታየው የአጋር ድርጅቶች ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመቀነሱ ነው ብለዋል፡፡
የበጀት ክፍተቱ በሥራው ላይ ጫና ሳይፈጥር የሀገር አቅምን ከማጎልበት ጎን ለጎን ከአዳዲስ አጋሮች ጋር የመፈራረም ሥራ እየተከናወነ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡
ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ለሆናቸው ሴቶች አገልግሎቱ እንደሚሰጥም ነው ያስገነዘቡት፡፡
በጎዳና የሚኖሩ ሴቶችን የጤና ፍላጎት ለማሟላትና ያሉባቸውን ችግሮች ለመቅረፍ የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር እንሠራለን ነው ያሉት፡፡
በኢትዮጵያ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር በ2000 ከነበረበት 6 በመቶ በፈረንጆቹ 2019 ወደ 41 በመቶ ማዳጉም ተመላክቷል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!