Fana: At a Speed of Life!

ዘመናዊ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎቶች እየተሰጠ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዘመናዊ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎቶች እየተሰጠ መሆኑን ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች ፥ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ 80ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ የሚካሄደውን አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት አስጀምረዋል::

በንግግራቸውም ፥ ተቋሙ በ1935 ዓ.ም ለ18 ተጋቢዎች ብቻ የጋብቻ ሁነትን በመመዝገብ አገልግሎቱን የጀመረ መሆኑን መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዛሬ ላይ ግን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎቶችን ተቋሙ እየሰጠ እንደሚገኝም ነው የገለጹት።

በአሁኑ ወቅት በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች ዘምነው እና ዲጂታላይዝድ ሆነው የሚሰጡትን አገልግሎቶች ሁሉ ከአንድ ማዕከል በማድረግ መረጃ መያዝ የሚቻልበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውንም ከንቲባዋ ተናግረዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.