Fana: At a Speed of Life!

ጤና ተቋማትን በማስፋፋት ምቹ የጤና አገልግሎት ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ጤና ተቋማትን በማስፋፋት ለሕብረተሰቡ ምቹ የጤና አገልግሎት ለመፍጠር እንደሚሰራ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ።

አቶ ኦርዲን ÷ በበጀት ዓመቱ በጤና ዘርፍ የተለያዩ መልካም አፈጻጸሞች ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸው÷ ከህብረተሰቡ ጥያቄና ፍላጎት አንፃር የተጠናከረ ስራ መስራት ይገባል ብለዋል።

በተለይም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማሻሻል ፣ የመድሃኒት አቅርቦት እና የመድሃኒት የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ ነው የጠቆሙት።

ብክነት እና ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ በትኩረት ይሰራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷የጤና ተቋማትን በማስፋፋት ለህብረተሰቡ ምቹ አገልግሎት ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ በበኩላቸው÷ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ መናገራቸውን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይ በመድሃኒት ፣በህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ፣ የጤና መረጃ ጥራት ማስጠበቅ፣ የጤና አገልግሎትን ፍትሃዊ እና ጥራት ያለው ለማድርግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.