Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ባላት የጋራ ጉዳይ ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ ናት – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ባላት የጋራ ጉዳይ ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ አቋም አላት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቴክኖሎጂ፣ በማዕድንና ቱሪዝም ላይ ኢንቨስትመንቶችን ማጠናከር እንዲሁም የንግድ ግንኙነትን ማጎልበት አስፈላጊ እንደሆነ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች ብለዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ አቋም አላት ሲሉም ነው የገለጹት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እና ሀያሺ ዮሺማሳን ከውይይታቸው በኋላ በአንድነት ፓርክ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.