Fana: At a Speed of Life!

የተበላሸ ብድር ምጣኔን 7 ነጥብ 1 በመቶ ማድረስ መቻሉን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት የተበላሸ ብድር ምጣኔን 7 ነጥብ 1 በመቶ ማድረስ መቻሉን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስታወቀ፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር)÷ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች ባንኩ ከኪሳራ ወጥቶ ውጤታማ ወደ መሆን እየተሸጋገረ ነው ብለዋል።

ለአብነትም ባንኩ የተበላሸ ብድር በማስተካከል ጤናማ መሆን እንዲችል የሚያስችሉ የለውጥ ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑን አንስተዋል።

የባንኩ የተበላሸ ብድር መጠን ከለውጡ በፊት 43 በመቶ እንደነበር ጠቁመው÷ በ2015 ወደ 7 ነጥብ 1 በመቶ ማውረድ ተችሏል ብለዋል።

ባንኩ በ2015 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም አስመዝግቧል ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ በዚህም ከታክስ በፊት 6 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ትርፍ አግኝቷል ብለዋል።

አሁን ላይ የባንኩ ካፒታል 38 ቢሊየን ብር እንደደረሰ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.