የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ ፈተናው ከኩረጃና ስርቆት በጸዳ መልኩ መሰጠቱን አንስተዋል፡፡
በፈተና ወቅት የተከለከሉ ቁሶችን ወደ መፈተኛ ቦታዎች ይዞ መግባት፣ የቡድን ፀብ ማንሳት፣ የፈተና ወረቀት ሳይመልሱ ለመውጣት መሞከርና መሰል ችግሮች መስተዋላቸውን ተናግረዋል።
በትግራይ ክልል በ2012 ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰድ ሲገባቸው ያልወሰዱ ተማሪዎች በቀጣይ ፈተና ላይ እንደሚቀመጡ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በቀጣይ መስከረም ወር የመልቀቂያ ፈተና እንደሚሰጥ ገልጸው÷አሁን ላይ የማጠናከሪያና የማካካሻ ትምህርት እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡
በታሪኩ ለገሰ