የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማርዲያት በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።
በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባርናባ ማሪያል ቤንጃሚን (ዶ/ር)፥ መሪዎቹ በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት፣ በኢኮኖሚ ትብብር እና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ዙሪያ እንደሚወያዩ ጠቁመዋል፡፡
ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።