35 ሺህ 870 ወገኖችን ከጎዳና በማንሳት የማቋቋም ሥራ መከናወኑ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 35 ሺህ 870 ወገኖችን ከጎዳና በማንሳት የማቋቋም ሥራ መከናወኑን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።
ወጪው በመንግሥት መሸፈኑንም በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ መላኩ ባዩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
እንዲሁም በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሐ-ግብር ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ 4 ሺህ 905 ወገኖች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በ8 ሺህ 630 ቀበሌዎች የድጋፍና እንክብካቤ ጥምረቶችን በማቋቋም እና ቀደም ብለው የተቋቋሙትን በማጠናከር ከ410 ሚሊየን 660 ሺህ ብር በላይ ከሕብረተሰቡ በዓይነትና በገንዘብ ተሰብስቧል ብለዋል።
በዚህም 89 ሺህ 12 ወገኖችን ባሉበት መደገፍ ተችሏል ነው ያሉት።
በዮሐንስ ደርበው