የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በሲዳማ ክልል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በሲዳማ ክልል ወንዶገነት ከተማ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና የችግን ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡
አመራሮቹና ሰራተኞቹ በወንዶ ገነት ከተማ ለሚገኘው ትምህርት ቤት 20 ኮምፒውተርና 3 ሺህ 500 መፅሐፍት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም አቅም ለአጠራቸው 1 ሺህ ለሚጠጉ ተማሪዎች የቦርሳ ድጋፍ እንዲሁም 700 ለሚሆኑ ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አበርክተዋል።
በዕለቱም የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሣ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እና ሌሎች ስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከሲዳማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡