Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ8 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ጥገና ስራ ተከናውኗል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል ከ8 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ጥገና ስራ መከናወኑን የክልሉ መንገዶች ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የእቅድ ዝግጅት እና ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር አሸናፊ ሃብታሙ እንደገለጹት÷ በ2015 በጀት ዓመት በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውን መንገዶች የመጠገን ስራ ተከናውኗል፡፡

በዚህም ከዞን ከተሞች እስከ ከጠር ቀበሌዎች ድረስ ያለውን የትራንስፖርት ፍሰት በተገቢ ሁኔታ ማሳለጥ መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡

በበጀት ዓመቱም በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸው 8 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መንገዶች ላይ የጥገና ስራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም 6 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነው መንገድ ከፌዴራል መንግስት በተበጀተ 530 ሚሊየን ብር በላይ የተጠገነ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ቀሪዎቹ መንገዶች ደግሞ ከክልሉ መንግስት እና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኘ ገቢ የተጠገኑ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የሚደርስባቸውን መንገዶች የመጠገኑ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ አሸናፊ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.